">ከፍቅር የበለጠ ሐያል ነገር የለም። ከጥላቻም ያነሰ ጉዳይ አላየሁም።
"Lamour's den" - Home Page Empty File untitled


እሁድ ቀን በምሳ ረፋዱ ላይ

በቢዩፈርድ ጎዳና በጠራ ሰማይ

መኪናዋን ይዤ ሳበራት ከላይ

ተዝናንቼ በጣም ከጤንነት ጋር

ጥሩ እንቅልፍ ኖሮ የሰላም አዳር

ምስጋና ላምላኬም ረስቼው ነበር

ለጠዋቷ ጠሀይ ለተፈጥሮ ዉበት

ለጥሩ ጓደኞች ፈገግታና ጥረት

ለሆስፒታል ነርሶች የስራ ውጤት

ምስጋና ለነሱ በጣሙን ስደሰት

ሙዚቃ እየሰማሁ መኪና ስነዳ

ፊቴንም ሲገርፈው የነፋስ ሽውታ

ጠሃይዋም ስትግል ወደ ጥላው ጠጋ

ፍጡራን ሲሮጡ ምቾትን ፍለጋ

ከሁሉም ትልቁን ረስቼው ኖሬ

በምቾት ስገበዝ ጥሬ ተፍጨርጭሬ

አገር ሰላም ብዬ በመኪና ፋታ

ስበር ስከንፍ ለመድረስ ባነዳፍታ

ድንገት ሃሳብ ገብቶኝ መንገድ ለመቀየር

የፊት ለፊትና የቀኙን መስተዋት

በማድረግ ቀኘት ደግሞም መልከት መልከት

የመንገዱን ሰላም በደንብ በማየት

ፍሬቻ አብርቼ ወደ ቀኝ ስታጠፍ

ከቁጥጥር ውጪ ሆና መኪናዋ እርፍ

በዛ ድንጋጤ በነበረው አጥናፍ

ቤተሰብ ጓደኞች በፊቴ እልፍልፍ

አቤቱ አምላኬ ምስጋና ይድረስህ

ነፍሴን አተረፋት ጠጋ ቸርነትህ

በጠዋት ለርካታ ለደስታ ለፍቼ

አየር ለመቀበል መስኮቴን ከፍቼ

የተፈጥሮን ውበት ሳደንቅ ተዝናንቼ

ያንተን ጥበብ ስራ ድንቅነት ረስቼ

ለሰው ደግነት ምስጋናን ሰጥቼ

ለህየወትም ጥማት በፍቅር ሳስቼ

አጃኢብ በመውደድ አልቄ ሟሙቼ

የውሃ ጥማቴን በቅጡ አርክቼ

ያንተን ጥበብ ስራ ድነቅነት ረስቼ

የመኪና ፍጥነት የደቂቃ ቅስበት

ህይወትና ሞት ደግሞም ጣፋጭ ህይወት

አቤቱ አምላኬ ምስጋና ይድረስህ

ነፍሴን አተረፋት ጠጋ ቸርነትህ፤ ፤

Web Hosting · Blog · Guestbooks · Message Forums · Mailing Lists
Allwebco Web Templates · Build your own toolbar · Site Building Articles · Audio, Fonts, Clipart
powered by a free webtools company bravenet.com