| ከፍቅር የበለጠ ሐያል ነገር የለም። ከጥላቻም ያነሰ ጉዳይ አላየሁም። |
|
|
የህይወት ቆንጆ ገጥታ
የወዳጀ ጠላት ፈገግታ
የጠላት ወዳጅ እርካታ
ያስተማሪ ተማሪነት
የተማሪ አስተማሪነት
የላዩ ታች ሲሆን
የታቹ ላይ መውጣት
ህይወት ስትመቻች
ህይወት ስትጎረብጥ
አበት ደስ ማልቷ
መራ መጣፈጧ፤ ፤
ያቺ ቅጥበት ለኔ
አወየው ኩነኔ
የጠራው ደፍርሶ
ደፍርሶ ሲጠራ
ቀን ሲጥል ሲያዋርድ
ህይወትም ጎርብጣ
ቀኑ ቀን ሲያወጣ
ጠላት ወዳጅ ሊሆን
ወዳጅ ሊሆነ ጣጣ
አዬ ህይወት ለኔ
አወየው ኩነኔ፤ ፤
bravenet.com