>






">ከፍቅር የበለጠ ሐያል ነገር የለም። ከጥላቻም ያነሰ ጉዳይ አላየሁም።
"Lamour's den" - Home Page Empty File untitled


ከስራ መጥቼ ደከም ብሎኛል

ምግብና ውሃ አስጠልተውኛል

ህይወት ወዲያ ወዲህ ትርጉም አጥቼበት

ትላንትና ዛሬም ኮምፒዩተር ትምህርት

እንደተለመደው ኢንተርኔት ገብቼ

ባህሩን ቀዝፌው በየብሱ ጠፍቼ

ኢትዮ ቻት ውስጥ ዘው አልኩኝ ለፍቼ

አቤት የስም ዐይነት እንዳው ለጉድ ነው

የደበራት አጅሬው ጎጃሜው ጎንደሬው

አጁ ስኳሯ ማሚ ቹና አስቀያሚው

ማሬ ወለላዬ ዱርዬ የኒውዮርክ አራዳው

በያይነቱ አለ ካልሰለቸው ለሱ

ስምን የሚመርጠው የሚያወጣው ራሱ

በ ኢንተርኔት ካፌ ጨዋታ ቢደራም

ኪቦረድ አደናቅፎ ከወሬ ባይጥልም

ዐይኔ ሲቀላውጥ የስም አይቶቹን

አንዷ ላይ አረፈ ዐይኔ ምስክንክን

ሚስ አቲቲዩድ ለራሷ ስም አውጥታ

አስደነገጠችኝ እኔን አርበትብታ

ለራሴ ቃል ገባሁ ባጠገቧ ላላልፍ

በስሟ በርግጌ እሷን ሳይ ስል እጥፍ

አንድ ቀን ደብሮኝ በ ኢንተርኔት ካፌ

ሳወራና ስስቅ እንዲሁም ሳዳምጥ

ሚስ አቲቲዩድ ገባች እያለች ገልመጥመጥ

አንዱ ጓደኛዋ ሰላምታ አስቀደመ

ደህና ነሽ ለጤናሽ? ብሎ ተደመመ

ደብሮኛል አለች አቲቲዩደኛዋ ሚስ

በማሳዘን ቃላት በለሰለሰ ድምጥ

ምን እንደው ሳላውቀው ልቤ ደከመባት

እጄም በኪቦርዱ ምን ሆነሽ ነው እያላት

እሷም እንዲያው በማሳዘን ሁሉን ነገረቺኝ

የየቀን ውሎዋን ትምህርቷን ድካሟን

ዘርዘር በማድረግ ዘከዘከችልኝ

በጥያቄና መልስ ስንመላለስ መሽቶ

ተግባባን መሰለኝ ጨዋታችን ደርቶ

ለማጥናናት ብዬ ልፍለፋዬን ጀመርኩ

እሷም ስታደምጠኝ ተዝናንቼ አለምኩ

ለካስ ስሟ እንጂ እሷስ ለስላሳ ናት

ቆንጆ የወፍ ርግብ እሷን ትውለድ እናት

እያልኩ ቀባጠርኩኝ በያዘኝ አባዜ

በቀን ህልም ላይ ኪቦርዱን ምርኩዜ

ትንሽ አወራነው አራምባና ቆቦ

ከዚህም ከዚያ ላይ ሃሳብ ተከናንቦ

ልቤም ደህና ሰንብች ብሏት አመስግኗት እሷን

ከ ኢንተርኔት ካፌ ጥፍት አለ እርሙን

አልፎ አልፎ ያያታል ካፌ ውስት ስትረብሽ

ሰላም ላንቺ ይሁንና ደህና ስንብትሽን

ጠይቆ ይረዳል ከዚያም እፎይ ይላል፤ ፤


Web Hosting · Blog · Guestbooks · Message Forums · Mailing Lists
Allwebco Web Templates · Build your own toolbar · Site Building Articles · Audio, Fonts, Clipart
powered by a free webtools company bravenet.com