>





ከፍቅር የበለጠ ሐያል ነገር የለም። ከጥላቻም ያነሰ ጉዳይ አላየሁም።
"Lamour's den" - Home Page Empty File untitled


የጠዋቷ ፍቅር የመውደድ ጤዛዋ

ረፈድፈድ አድርጋ ጠፋች ከደብዛዋ

አገር ሰላም ብዬ መውደድን አቅፌ

ፍቅር ተመችቶኝ ስፈግ በንቅልፌ

መቼ ዋዛ ሆና የመውደዴ ሌባ

ፈትለክ ብላ ጠፋች ፍቅሬን ተከናንባ

መውደዴ ሌባዋ ፍቅሬን ነጥቃ ሄደች

ኑሮ ትምርት ብላ ካለፎርኒያ ገባች

ልቤ በሩን ዘጋው ለፍቅር ለመውደድ

ሊያገግም ሊያስታምም ስብራቱን በደንብ

መውደድ ያፋፋው ልብ ችግር ያልደፈረው

ፍቅሩን ሲነጠቅ ቆሳስሎ አረፈው

መውደዴ የት ሄደ ከጠየቀች ምንአልባት

መውደድ ገደል ገባ ብላችሁ ንገሯት

የመውደድ ድሪቶ በቤቴ ተለብሶ

የፍቅረ ቡቱቶ በወረት በስብሶ

ዕራቁት አስቀረኝ ፍቅርም በኔ ብሶ

ድሪቶም በቦታው ቡቱቶም በቦታው

ሰብስቤ ለገደል እንዲያው ጥቅም የለው

መውደዴ የት ሄደ ከጠየቀች ምንአለባት

ፍቅር ገደል ገባ ብላችሁ ንገሯት

እንደልማዳቸው አበው ሲተርቱ

ሁሉም ይመለሳል ወደ መሰረቱ

የወጣም ይወርዳል የመጣም ይሄዳል

የጣፈጠም ሲመር

የላላው ሲከርር

ዛሬ የተጠላው በሁዋላ ሲፈቀር

የታመመው ሲድን ህመሙ ሲሰበር

ላጤውም ሌጣውን ሌላውም ከሚስቱ

እንደልማዳቸው አበው ሲተርቱ

ሁሉም ይመለሳል ወደ መሰረቱ፤ ፤

መውደዴ የት ሄደ ከጠየቀች ምንአልባት

መውደድ ገደል ገባ ብላችሁ ንገሯት፤ ፤

Web Hosting · Blog · Guestbooks · Message Forums · Mailing Lists
Allwebco Web Templates · Build your own toolbar · Site Building Articles · Audio, Fonts, Clipart
powered by a free webtools company bravenet.com