|
|
| Welcome to Demis's island-Kick back and relax...laugh love live |
ሜትር እንካ
ሂድ ተነስ
ትችት ቀንስ
ንዳ ብረር
ስራው አይቀር
ሆኑአል ምሱ
ጊዜ ትራሱ
የላብ ምጣጭ
ህይወት ; ጣፋጭ.....ብለናል።;
አቀረሸኝሳ
ወተቴን በጠጣሁ
እራቴን በበላሁ
ፍቅር ጨምሬበት
እኔ ባንቀላፋሁ
ነገ ዛሬ ሆኖ
በትናንት ሳቀሳ
ምነው ሁሉ ነገር
አቀረሸኝሳ።
ካርማ
ሳልሰራ ደክሜ
በጤና ታምሜ
ስንፍናን አንግቤ
ለራስ ተስገብግቤ
በባዶ ጠግቤ
ሳልነግድ ከስሬ
ሳልጠጣ ሰክሬ
ሳልተኛ አለምኩኝ
ሳልጀምር ደረስኩኝ
ሳልገዛው ወስጄ
እብደቱን አብጄ
በልቤ ቀንቼ
የሩቅ ተመኝቼ
ጠላቴን ጠልቼ
ለነገ ሰስቼ
ሳልቀርብ መራቄ
ተኩራርቼ ንቄ
ሳይዘልፉኝ ዘልፌ
አበባ ቀጥፌ
ካርማዋ ሳመቺኝ
እኔነቴን ጠልታ
እኔን ወደደቺኝ።
bravenet.com