| ከፍቅር የበለጠ ሐያል ነገር የለም።
ከጥላቻም ያነሰ ጉዳይ አላየሁም።
|
"Lamour's den" - Home Page
Empty File
untitled
ቀዝቃዛዋ ቤቴ ትቀዘቅዛለች
አጥንት አደንዝዛ ዋ ሆይ ታሰኛለች
ከስራ ስመለስ ደክሞኝ ወደ ቤቴ
የብርዱ ትውስታ ድቅን ብላ ፊቴ
ፊልም ቤትም ሄጄ ፊልሜንም አያለሁ
ሌሊቱ ቢጋመስ ብዬም አስባለሁ
የቤቱን ማሞቂያ ልገዛም አስቤ
ላንድ ሳምንት ችግር ምነው አለኝ ልቤ
እረፍትን ለማግኘት ከቤቴ ገብቼ
ገላዬነ ታጥቤ ጣጣዬን ጨርሼ
ለሃያሉ ጌታ ምስጋናን አድርሼ
ጋደም እንዳልኩና ሸለብ እንዳረገኝ
የመኪና ጥሩንባ ደርሶ ቀሰቀሰኝ
ጎረምሶች ሙዚቃ አርብ ሌሊት ላይ
ጉአደኛ ይጣራል ጎረምሳው ያፉአጫል
ጉአደኛ ለመውሰድ መኪናው ይዘፍናል
እሱ ምን ቸገረው ህዝብ አዳም ተኝቷል
ከኔ ክፍል በላይ ያለው ጎረቤቴ
ይንጎራደዳል እቃ ያንጎዳጉዳል
ይህን ጊዜ ነው ብርዱ ሰፍሰፍ የሚያረገኝ
የቤቴ ቆፈንም የሚቀዘቅዘኝ
ያቺን ደመ ሞቃት ትውስ የሚያስብለኝ
ደመ ሞቃቷማ ሸገር ላይ ቀርታለች
እኔን ለትዝታ ለፍቅር ስጥታለች
እሷን በትዝታ ጋቢ ሳቅፍ ሳሽሞነሙን
ዐይኗን ከንፈሯንም ስስም በሰመመን
ሰውነቴ ሲሞቅ ሲግል ደስ ሲለኝ
የመኪና ክላክስ ደርሶ ቀሰቀሰኝ
ሌላው ጎረምሳ ነው ለከንፈር ወዳጁ
ጥሪ ማቅረቡ ነው እሱም በየፈርጁ
ያርብ ማታ ጉዳይ መች ሆነ ነገሩ
የየቀን ሆነና ሰውን ማሰቸገሩ
ስኞ ማክሰኞ ጧት ረቡዕና ሃሙስ
ልማድ አድርጎታል አጅሬ መቀስቀስ
ያላወቀው ነገር ያልተረዳው ቢኖር
ወዳጅ ሲቀሰቅስ መበጥበጡን ነበር
በሱ ወዳጅ ስበብ ከ እነቅልፌ ስባንን
ሰናደድ ስራገም ዐይኔን ሰጨፋፍን
እስከመቼ ብዬ ለመልቀቅ ስወስን
ጊዜን አሰላሁት አንድ ሁለት ሶስት
ሮጧል መንኗል ሞልቷል አራት ሳምንት
ያንድ ወር ታዛዬ ቀዝቃዛዋ ቤቴ
በይ ደህና ሁኚልኝ ለኔ ራስ ምታቴ
አልሰማሽም ወይ የፔፕሲን ተረት
ኑሮ ከተባለ የፍሪጅን ሙቀት
ያንቺ ቅዝቃዜ ከፍሪጅ ባሰና
እኔን አስመረረኝ ቆፈነነኝና
እናማ የኔ ቤት ፍሪጇ ደህና ሁኚልኝ
ለምትቀጥለዋ መልክቴን ስጪልኝ
የቤት ማሞቂያውን ይዛ እንድትገባልኝ፤ ፤