| ከፍቅር የበለጠ ሐያል ነገር የለም።
ከጥላቻም ያነሰ ጉዳይ አላየሁም።
|
"Lamour's den" - Home Page
Empty File
untitled
አቤቱ አምላኬ እንዴት ፈጥረሃታል
አቆነጃጅተሃት አሳምረሃታል
ያይኖቿ ማማር የከንፈሯ ውበት
ያፍንጫዋ መርዘም የጉንጮቿ ፖምነት
የቅርጧ መጠረብ የጠጉሯ ዞማነት
በፍጥረት አለሙ ያላት አስተያየት
ያላት እርጋታና ለዛ ቀልደኛነት
ድምጠ መልካምና መረዋ አንደበት
አቤቱ አምላኬ እነዴት ፈጥረሃታል
አቆነጃጅተሃት አሳምረሃታል
አምላኬ ጊዜውን ያጠፋባት ቆንጆ
በጣሙን ታምራለች ደግሞም ታሳሳለች
ስራዋን አክባሪ ሰውነ ትወዳለች
ወዲያ ወዲህ ስትል ለስራ ተፍ ተፍ
አዳሜ ጎረምሳ አብሯት ሲንሰፈሰፍ
እሷ ግን ስራዋን ታሰላስላለች
ለሁሉም ጊዜ አለው ብላ እያሰበች
ለሚጎነትላት ይህንኑ እያለች
አቤቱ አምላኬ እንዴት ፈጥረሃታል
አቆነጃጅተሃት አሳምረሃታል
እንከን አይወጣላት ላለባበሷ
ስትራመድ እንኳን ጠጉርዋን መነስነሷ
ስታወራ ስትስቅ ስትፈለቅቅ ጥርሷን
ዐይኗንም ስልምልም ደግሞም ጨፈን ከደን
የክፍል ፕሬዚዳንት ተብላ ተሹማለች
ሙያተኛ ተብላ ስምም ተሰጥታለች
ትምህርቷን በሙሉ በመቶ አልፋለች
ያመቱ ኮኮብም ተብላ ተጠርታለች
ምስጉን ሰራተኛ ሆና በስራዋ
ሽልማት አግኝታ ለጥሩ ሙያዋ
የጓደኞች ውጤት ብላ በትህትናዋ
ዕድሜ ለናንተ ነው ለባልደረቦችዋ
አቤቱ አምላኬ እነዴት ፈጥረሃታል
አቆነጃጅተሃት አሳምረሃታል
ስድስት ወራት ሙሉ ተመልክቻታለሁ
በጥሩ ፈገግታ ሰላም ብያታለሁ
ሳልፍም ሳገድም አሳስቄያታለሁ
በቡና ዕረፍቴም አዋርቻታለሁ
ለሻይ ምሳ ግብዣ አግደርድሬያታለሁ
አቤቱ አምላኬ እንዴት ፈጥረሃታል
አቆነጃጅተሃት አሳምረሃታል
ሁኔታዋን ሳየው በደንብ ወዳኛለች
ከሌሎቹ ሁሉ እኔን አቅርባለች
እንደመሰለኝም ልቧን ሰጥታኛለች
ልብሽን ውሰጂው ስጪኝ ስልክሺን
በማለት ጠየኳት ቆንጂት እባክሺን
ሌላ ሌላ ነገር ግድ የለም ይሁን
ለስልክ አላገኝም ፈቃድ የባሌን
ብላኝ አረፈቺው የኔዋ ቆነጂት
የሰው ጥጌሬዳ የሰው እመቤት፤ ፤