>






ከፍቅር የበለጠ ሐያል ነገር የለም። ከጥላቻም ያነሰ ጉዳይ አላየሁም።
"Lamour's den" - Home Page Empty File untitled


የትናንቷ ውዴ ፍቅሬ አለኝታዬ

የዛሬ ባዳዋ የሩቅ እንግዳዬ

የነገ ትዝታ ህልምና ቅዠቴ

እርሺኝ ረሳሁሽ የታሪክ ትዝብቴ

እኔ ትላንትናን አንቺ ዛሬን ሆነሽ

ነገ ሊያመልጠን ነው አላስታውስ ብለሽ

የትላንት አበባ ፍቅር ንጥህና

አላየሽም አንቺ የዛሬ ግድግዳ ሸፍኖሻልና

የትናንት ቡቃያ ለዛሬ ፍቅር ነው

ለነገ አበባ የቤት ማስጌጫ ነው

የቡቃያው ጌሾ ዛሬ በሰበሰ

የፍቅር ቅራሪው ተከላለሰ

የትዝታ እሳት በልቤ ተዳፍኖ

አይኔንም ሸፈነው የፍቅር ጭስ ሆኖ

ዛሬም አልወጣ አልኩኝ ሰንፌ በጣሙን

ከትናንትና ወዲያ ፍቅር ብዬ ለምን

ነገማ ጨለመ ምንም አይታየኝ

ዙሪያው ገደል ሆኖ ተደነጋገረኝ

በሽታም ህመሜም ቁርጥማቴም ሆነሽ

ያለ ምንም ምክነያት ዱታ ነኝ ማለትሽ

ሰማሽ ወይ የኔ ሆድ ሰሚ ለኔ ብለሽ

የትላንቷ ፍቅሬ ዛሬ ስታዘብሽ

አጃኢብ ሞኝነት ለካ አንቺም ሰው ነሽ

ፍቅሬ ሆይ ይመችሽ ተደላደይበት

ካሁን ወዲያ አይኔም ሌላዋን ይይበት

አንቺ ለኔ አልሆንሽም እኔስ ምን ጨነቀኝ

ለፍቅር ብዬ እንጂ ያንቺ እዳ የለብኝ

አልመስለኝ ብሎ ነው ፍቅር ካንቺ ሌላ

መሞኘቴን ሁሉ ያወቅሁት በሁዋላ

ዛሬማ እንግዲህ ዐይኔን ከፍቻለሁ

ዕድሜ ለጓደኞች ፍቅርነ አግኝቻለሁ

ወድጄሽ ነበረ አምልኬሽ ተጃጃልኩ

ጠባይሽን አድንቄ ሰውነትሽን ረሳሁ

ጥሩ ህልም ነበርሽ ከንቅልፌ ነቃሁ

ሰማሽ ወይ ቅድስቴ ስሚ ለኔ ብለሽ

ያለ ምንም ምክንያት ዱታ ነኝ ማለትሽ

ለኔም ግራ ገባኝ ሰሚውም ጉድ አለሽ

ልቤም ዘንግቶሻል አንቺን እንዳላለሽ

አጃኢብ ሞኝነት ለካ አነቺም ሰው ነሽ፤ ፤


Web Hosting · Blog · Guestbooks · Message Forums · Mailing Lists
Allwebco Web Templates · Build your own toolbar · Site Building Articles · Audio, Fonts, Clipart
powered by a free webtools company bravenet.com