| Welcome to Demis's island-Kick back and relax...laugh love live |
"Demis's den" - Home Page
Empty File
untitled
ጊዜው ከነፈ በረረ አለፈ
ትዝታሽን ጥሎ ክፉነትሽን መንትፎ
ላይመለስ ትናንትን ሆኖ
ላይያዝ እንደ ደመና ጉም በንኖ
ትናንትና አልፎ ሳምነት ሆነ
ትዝታሽ አንቺን አገነነ
ዛሬም ሲነጋ ጆሮዬ ሲቋምጥ
ያንቺን መረዋ ድምጥሽን ሊያዳምጥ
ሲያምርህ ይቅር ብለሽው ይሆን
እኔነቴ የተከፋውሰምቶ ልቤን
ሆዴም የባባው ዐይኔም ዕንባ ያቀረረው
ፈገግታሽን ሲያጣ ምስልሽን ሲመለከት
እንዴት ውላ ይሆን ሲልና ሲዋትት
ልቤም ሲያስብ በልቡ ያለኔ አይሞላልሽ
አላግጠሽ አያ ጅሎ ብለሽ
ሄድሽው እንደዘበት ተመቻችተሽ
የኔ ቆንጆ የኔ ፍቅር የኔ ሆዴ
ደላሽ ወይ ተመቸሽ ኑሮን ለመድሽ እንዴ
ከንግዲህማ በርቺ አንቺው ላንቺው
ኑሮም ብርዱ ብርዱም ነው ኑሮው
ቢያስቸግርሽ እንኳ ቢያቆፈንንሽ
የትዝታን ፍቅር ጋቢውን ልበሽ
እኔማ ያላንቺ እንዳለሁ አለሁ
በፍቅር እጦት እያነባሁ
በትዝታ ናፍቆት እያነጋሁ
ጠዋት ማታ አለቅሳለሁ።